በየት በኩል ሐይቅ እንደገቡ ያልታወቀ 19 የሕወሓት ታጣቂዎች ውስጥ 18ቱ ተደመሰሱ | ሆኖም ሃይቅ ልዩ ትኩረት ይፈልጋል | የአካባቢው ነዋሪ ቤቱን ጥሎ መሄዱን ሊያቆም ይገባል

 

በየት በኩል ወደ ሐይቅ ከተማ እንዳልገቡ ገና እየተጣራባቸው ያሉ 19 የሕወሓት ታጣቂዎች መካከል 18ቱ መደምሰሳቸውን የዘ-ሐበሻ የመከላከያው ምንጭ አስታወቁ። ሆኖም ግን የአካባቢው ነዋሪ ሐይቅን እየለቀቀ እየተሰደደ መሆኑ ለሕወሓት ዝርፊያና መስፋፋት ጥሩ ዕድል ሊሆን እንደሚችል ምንጩ አክለዋል።

በሐይቅ ቁልቋሎ፤. አሚናምባ እና ቀጤ አካባቢ የመጣው የጁንታው ኃይል ጋር ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮቹ በነዚህ አካባቢዎች ነዋሪዎች ለቀው በመውጣታቸው ሕወሃት ለመዝረፍ ተመችቶታል ብለዋል። እቃዎችን እየዘረፈ እየጫነ ነው የሚሉት ምንጮቹ የኢትዮጵያ ኃይሎች ይህንን ወራሪ ኃይል ከነዘረፈው ሊጥና አሻቦ እዚያው ለመቅበር ተጋድሎ እያካሄዱ መሆኑን ነግረውናል።

እነዚህ 19 የሕወሓት ታጣቂዎች በአዲስ ሰፈርና በሆስፒታል መንገድ እየተታኮሱ የነበረ ሲሆን 18 ሲገደሉ 1ኛው ተማርኳል። ሕዝብ ኃይቅን ለቆ መውጣቱን እንዲያቆም ጥሩዎች ቀርበዋል።

 

በደቡብ ወሎ ተሁለደሪ ቀበሌ 09 አሙሞ የሚገኘው መስጊድ ላይ ሕወሓት ከባድ መሳሪያ ከርቀት በመተኮስ መስጊዱን ሲያወድም በመስጊዱ ውስጥ የሚያሰገዱ አንድ የሃማኖት አባት መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል። እንዲሁም የቅዱስ ቁር አን መምህራን የሆኑ 2 ሰዎችም በዚሁ ጥቃት ሕይወታቸው እንዳለፈ ከስፍራው የመጣው መረጃ አመልክቷል። በመስጊዱ ላይ ሕወሓት በከባድ መሳሪያ ባደረሰው ጥቃት እስካሁን የሞቱት 3 መሆናቸው ይረጋገጥ እንጂ ቁጥሩ ከፍ ሊል እንደሚችል ተነግሯል።