የፊታችን ሰኞ የሙስና ክስ ሊመሰረትበት ክስ የተጠናቀቀበትን የሕወሓት ባለሃብት ሙሉጌታ ፒፓን ክሱን አሰርዞ በዋስ ለማስፈታት እየተሰራ ነው ተባለ

ከአሜሪካ ቦስተን ከተማ ፓርኪንግ ሰራተኛነት ተነስቶ በፍጥነት የነስብሃት ነጋን ገንዘብ በማንቀሳቀስ እጅግ ሲበዛ ሚሊየነር እንደሆነ የሚነገርለት ባለሃብቱ ሙሉጌታ ፒፓን ከእስር ለማስለቀቅ በመንግስት ውስጥ ያለ ህቡዕ መዋቅር እየሰራ መሆኑ ተጋለጠ።

ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት የሕወሓት ዋና የገንዘብ ምንጭ ባለሃብቱ ሙለር ፒፓ (ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ) የፊታችን ሰኞ የሙስና ክስ ሊመሰረትበት በዝግጅት ላይ ነበር።  ማስረጃዎች ተሰባስበው ክስ ተዘጋጅቶ ሰኞን እየጠበቀ ቢሆንም፤ ከባለሃብቶች፣ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሰራተኞች፣ ከፖሊሶች እና ከዳኞች ጋር የተያያዘው አንድ ሕቡዕ ቡድን የሙስና ክሱን አስቁሞ በዋስ ሊያስለቅቀው እየሰራ እንደሆነ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል። 

ይህ ህቡዕ ቡድን ኪሱ ከሞላ የሃገር  ጥቅም የሚባል ነገር የሚገባው አይደለም የሚሉት ምንጮቹ መንግስት ይህን በውስጡ የተሰገሰገ ጁንታ ካላስቆመው ሙሉጌታ ሰኞ በዋስ ሊለቅ እንደሚችል ነግረውናል    

   ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ  በ1960ዎቹ በሱዳን አድርገው ወደ ጀርመን ሃገር በመሄድ እዚያ ለህወሃት ትግል የሚረዳ ገንዘብ ይሰበስቡ የነበሩ ባለውለታ ናቸው። በ1977 በተከሰተው ርሃብ ከቦብ ጌልዶፍ ጋር “ባንድ ኤይድ” የሚል የሙዚቃ ኮንሰርት ውስጥይ እጃቸው አለ። ከተገኘው 100 ሚሊዮን ዶላር 90 በመቶው ለወያኔ ተሰጥቶ፣  35% ያህሉ ለወታደራዊ መሣሪያዎችን እና መገልገያዎችን እንደዋለ ቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ለሕዝብ ይፋ አድርጎታል።

    ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ከስብሀት ነጋ ጋር በጋብቻ ይዛመዳሉ። የብር ጎተራ የሰሩትም በዝርፍያ የተገኙ የስብሃት መንግስት ሃብት ለማጠብ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል። በብርሃን ፍጥነት ድህነትን አሽቀንጥሮ የመጣሉ ምስጢር ይኸው ነው። ሃብት ያካበቱት በሎተሪ ወይንም በስራ ተነስተው አይደለም። ከዚያ ድህነት እና ቅፈላ ተወንጭፈው ቢሊዮነር ከሆኑ የህወሀት ቀኝ እጆች ውስጥ አንዱ ናቸው።

          አዛውንቱ ስብሃት ልማት ባንክን እንደ ጥገት ላም እንዲያልቡ ሰርተፊኬት እንደሰጧቸው የሚነገርላቸው ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ለሀገረ ሰላም ኩባንያ 150 ሚሊየን ብር ወስደዋል። ለሁዳድ ድርጅት ደግሞ 250 ሚሊየን ብር ከባንክ ተሰጥቷቸዋል። በአፋር ክልል ሰመራ የጨው ማቀነባበሪያ በሚል 2.9 ሚሊየን ብር ተበድረው ገንዘቡን በስራ ላይ አላዋሉም። በለገጣፎ ለሪል እስቴት በሚል 500 ካሬ ሜትር መሬት ያለአግባብ ተሰጥቷቸዋል። መክሊት PLC. በሚል የቢሮ እና ኮንስትራክሽን እቃዎችና ለመንግስታዊው መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን እያከራዩ በዓመት 30 ሚሊየን ብር ገቢ ያደርጋሉ።

          አዋሽ የወይን ጠጅ ፋብሪካን በወደቀ ሂሳብ ገዙት። ከሚታወቁበት ሙለር ሪል እስቴት በተጨማሪ አካካስ ሎጂስቲክስ፣ አካካስ ሪል እስቴት፣ ሲምቦ ላንጋኖ ቢች፣ ብሉ ናይል ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ኩባንያዎችን በግል ንብረትነት ያስተዳድራሉ።

          ከትህነግ መታበቅ የጠቀማቸው አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካን ያለ ምንም ጫረታ እጅግ በወረደ ዋጋ መግዛታቸው ብቻ አይደለም፣ በብዙ ጥረት የተገኘውን የአቶ በቀለ ሞላን አንጋፋ የላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴልን ነጠቃ በሚመስል መንገድ ወስደው የግል አድርገዋል።

       ሙለር ከሰሩት ከባባድ ታሪካዊ ውንጀሎች አንዱ የአርበኛ ራስ አበበ አረጋይን ታሪካዊ መኖርያ ቤት ከባለስልጣናቱ ጋር በመመሳተር ናፍረሳቸው ነው። በአዋሬ በአድዋ መንገድ የሚገኘውን ታሪካዊው ቅርስ  በአራት ሚሊዮን ገዝተው፣  በደስታ ሲያፈርሱት ለታሪክ እና ለሃገር ፍቅር አንድም ደንታ የሌላቸው መሆኑን አስመስክረዋል። ራስ አበበ አረጋይ ቤት፣ ባህልና ቱሪዝም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉ ‘ታሪካዊ ቤቶች’ ብሎ ከያዛቸው ከ400 በላይ ቅርሶች አንዱ እንደነበር ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም።