ሕወሓት የሚተማመንበት አጋዚ ቁጥር 2 ኮማንዶ ተመታ

 

ሕወሓት እተማንበታለው እያለ በስፋት ስለጀግንነቱና ገድሉ ሲለፍፍለት የነበረው አጋዚ ቁጥር 2 ብርጌድ ኮማንዶ ወደ ሐይቅ ከተማ እየተጠጋ በነበረበት ሰዓት በኢትዮጵያ ኃይሎች አከርካሪው ተመታ። በዚህም የአጋዚ ብርጌድ ኮማንዶዎች መካከል አብዛኛዎቹ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን የሚናገሩት የመከላከያው ምንጭ ወደ ጊራና እና ወረባቢ የቀሩት በፍርሃት እያዝረጠረጡ መሸሻቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በዚያ አካባቢ ተመልሰው ሊደራጁ ስለሚችሉም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ምንጪቹ ተናግረዋል። በሌላ በኩልም በተሑለደሬ ሐይቅ አካባቢ ሽንፈት የገጠማቸው የሕወሓት አባላት ወደ ሐብሩ ድሬ ሪቃ ሰዶማ አካባቢ በፍርሃት በመፈርጠጥ ያመለጡ ሲሆን ድሬ ድሮቃ ሰዶማ አካባቢ መሳሪያዎቻቸውን በመሸጥ እየጠፉ መሆኑ ተናግሯል። የአካባቢው ማህበረስብ ወደሕዝብ መሳሪያቸውን እየሸጡ የሚገቡት ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለበትም የጥንቃቄ መል ዕክት ተላልፏል።