ጠፍተው ከሃገር የወጡ የሕወሓት አመራሮች በድንበር አካባቢ በሱዳን ጦር ታጅበው ቅኝት ሲያደርጉ ዋሉ

የትግራይ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበረውና ከጦርነቱ በኋላ ሱዳን ሸሽቶ የገባው ተኪኡ ማዕሾ፣ ሰባሆ፣ ግደይ፣ ኮለኔል ገብረ እግዚአብሄር ከቦስተን ተነስቶ ከሄደው ስዬ አብርሃ ጋር በመሆን ከበረከት ከተማ 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሱዳኗ ገሪባ ከተማ በመምጣት ጥናት ሲያደርጉ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ።

Tekiu Measho (Photo: TPLF Official)

ገሪባ ከተማ ከፍተኛ የሱዳን ጦር ሰራዊት ያለበት ሲሆን ወደ ሉግዲ ድንበር ወታደራዊ ጥናት ሲያደርጉ እንደነበር የሚገልጽቱት እነዚሁ ምንጮች በአካባቢው የነበረው 2 ሻምበል የአማራ ልዩ ኃይል ወደ ሌላ ቦታ መልቀቁን መሰረት አድርጎ አዲስ አቀማመጥ ካለ ለማጥናትና መንገዶች ካሉ ለማየት ነበር የቅኝቱ አላማ። በስፍራው የነበረው የአማራ ልዩ ኃይል ወደ ጭልጋ ሄዷል መባሉን ተከትሎም እነተኪው እና ስዬ አብርሃ ጥናቱን ቀጥለውበት እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች በዚህ አካባቢ እንቅስቃሴ ቢጀምሩ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ሊደርስባቸው ስለሚችለው ጥቃት ሲነጋገሩ ነበር ተብሏል።

በሱዳን ጦር ታጅበውው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የመጡት የጁንታው አመራሮች ሉግዲ፣ መቻች አቅጣጫ የአብደራፊ መስመር እና የማይካድራ አዋሳኝ በካርታ ላይ የጀመሩት እቅድ መሬት ላይ ለማውረድ አካባቢውን ስለማያውቁት ነው ቅኝት ማድረጉ ያስፈለገው።

በዚህ አካባቢ ሲንቀሳቀሱም ከኢትዮጵያ መከላከያ ሊደርስባቸው ስለሚችለው አደጋ ስጋት ደረጃም ሲነጋገሩ፤ በስፍራው ኦፕሬሽን መጀመር ለአውሮፕላን ድብደባ አመችነት ስለማጋለጡ ፣ ለከባድ መሳሪያድብደባ ሜዳ ላይ ያለው ጠቀሜታ እና የልዮ ኮማንዶ ከአውሮፕላን ዘሎ ሊፈፅመው የሚችለው ጥቃት በስጋት አንስተው ሲነጋገሩበት እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል።

እነተኪኡ የሱዳን ስልክ መያዛቸውንም መረጃዎች አመልክተዋል።

የትግራይ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበረውና ከጦርነቱ በኋላ ሱዳን ሸሽቶ የገባው ተኪኡ ማዕሾ የፌደራል ፖሊስ የዕስር ማዘዣ ካወጣባቸው የሕወሓት ዋና አመራሮች መካከል አንዱ ነው። እንዴት እና መቼ ሱዳን ሸሽቶ እንደገባ እስካሁን አይታወቅም። ተኪኡ ከመቀሌ ሆኖ የጌታቸው አሰፋን ትዕዛዝ በመቀበል በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች የሽብር ተግባራትን ሲያስፈጽም እና ሲያደራጅ እንደነበር የፌደራል ፖሊስ በቅርቡ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም ላይ አሳይቷል።

ነዋሪነቱ ቦስተን አሜሪካ የሆነው ስዬ አብርሃ ወደ ሱዳን አቅንቶ የነበረው ለቀናት ብቻ እንደነበር ምንጮች ይገልጻሉ። ስዬ አብርሃ ከዚህ ቀደም ወደ ሱዳን ድንበር ሄዶ እንደነበርም ተወርቶ የነበረ ቢህንም እርሱ ግን ከቦስተን እንዳልወጣ ሲናገር ቆይቷል።