የደቡብ ሱዳን የጤና ሀላፊዎች በጎረቤት አገር ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ መሄዱ እንዳሳሰባቸው አስታወቁ፡፡

የደቡብ ሱዳን የጤና ሀላፊዎች በጎረቤት አገር ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ መሄዱ እንዳሳሰባቸው አስታወቁ፡፡ የአፍሪካ ኒውስ ኔትወርክ እንደገለፀው በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ከምንጊዜውም በበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በቫይረሱ ተይዟል፡፡ የደቡብ ሱዳን የጤና ሀላፊዎች ይህ ጉዳይ እንቅልፍ እንደነሳቸው ለዜና አውታሩ አስረድተዋል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ከአዲስ አበባ ጁባ የሚበር መሆኑ ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ሱዳን የጤና ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቶዩ ሲንጎት ይህ በረራ በከፍተኛ ጥንቃቄ መቀጠል እንደሚገባው ማሳሰባቸውን የዜና ምንጩ ጨምሮ ዘግቧል፡፡