ከሱዳን ሰርገው የገቡ ጥምር የህወሓትና ቅማንት ኃይሎች በሳራባ ካምፕ ታሰሩ | መከላከያው እና የአማራ ልዩ ኃይል ሽፍተውን ኃይል ከአይከል ጭልጋ መተማ መንገድ ጠራረጉ | አንድ ቀብሌ ብቻ ይቀራቸዋል

(ዘ-ሐበሻ) ከሕወሓት ጋር ተባብሮ በሱዳን ሰልጥኖ በሱዳን ኮሎኔሎች እየታዘዘ ጭልጋ ከተማ በመግባት በአማራ ልዩ ኃይል ካምፕ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሃገር ለመጠብቅ ያስቀመጣቸው ወታደራዊ መገልገያዎች ላይ ጥቃት የፈጸመው የቅማንት/ሕወሃት ሽፍታ ቡድንን የምጻዳቱ ተል ዕኮ እየተገባደደ መሆኑን አንድ የዘ-ሐበሻ ምንጭ ገለጹ። ከመተማ እስከ ጭልጋ አይከል ድረስ ለቀናት ተዘግቶ በነበረው መንገድ የተነሳ  በመከላከያው ታጅበው ይንቀሳቀሱ የነበሩ መኪኖች አሁን ላይ ወደ ቀድሞው ተግባራቸው እየተመለሱ መሆኑን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

የቅማንት ተወላጆች “በጭልጋ የተፈጠረው ችግር እኛን አይወክልም!!” በማለት አቋማቸውን ከገለጹና ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበራቸው ከህወሓት ጋር አብሮ የመጣው የሕወሕት ጉዳይ ፈጻሚውን የቅማንት ታጣቂ ነኝ ባይ አሳልፎ በመስጠቱ መከላከያው እና የአማራ ልዩ ኃይል የተሳካ ተለእኮ እንዲፈጽሙ አስችሏል ተብሏል።

ኮሚሽነር ደስየ ደጀን በሚመሩት የአማራ ልዩ ሀይል እና መከላከያው ክልሉን ለማተራመስ  የተከፈተበትን መነሻው ሱዳን ያደረገው ወንበዴ ቡድና ቅትረኞቹ የቅማንት ኮሚቴ አብዛኛወች ተደምሰዋል ያለው ምንጩ፤ አሁን ሁሉንም አካባቢዎች አጽድተው የቀራቸው  ርቤት የተባለች ቀበሌ አካባቢ ያለው ኃይል ነው ብለዋል። በርካታ የሕወሓትና ቅማንት ታጣቂዎችም በቁጥጥር ስር ውለው በሳራባ ካምፕ እንደታሰሩም የዘ-ሐበሻ ምንጭ አክለዋል።

የአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ትንኮሳዎች እየተፈጸሙበት ነው፤  ልዩ ሀይሉና መከላከያው መሳዎትነት እየከፈሉ ህግን ለማስከበር ሕዝቡ አንድነቱ ጠብቆ እንዲጓዝ እያደረጉ ነው የሚሉት አንድ የአማራ ልዩ ኃይል የዘ-ሐበሻ ምንጭ የመተማ መንገድ ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር በንግድ የሚያስተሳስር ትልቅ የንግድ በር ነው። በዚህ በር ላይ ጥቃት በመሰንዘር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ልማዳከም የሚደረገውን ማናቸውንም ጥቃት አንታገስም፤ አሁንም በዚህ መስመር የሰፈረውና ሰላም ሲነሳ የቆየውን ኃይል ደምሰሰን የቀረን ሮቢት ቀበሌ ያለው ኃይል ነው እርሱንም እናጸዳዋለን ብለዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በአዳኝ አገር ጫቆ የሚኖረው ህዝብ ሰሞኑን ባደረገው ስብሰባ  ቅማንትና አማራ አንድ ሕዝብ ነው ምንም ልዩነት የለውም ከሕወሓት ጋር አብሮ የመጣው ኃይል በቅማንት ስም የሚላላክ ተላላኪ እንጂ የኛ ወገን አድየለም ሲሉ ማውገዛቸው ይታወሳል።